```blade ``` የስልጢ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሸምሴ ረዲ በወረዳው አሹቴ ቀበሌ በዳያስፖራው በተሳትፎና ድጋፍ እየተገነባ የሚገኘውን የአሹቴ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የቤተ-ሙከራ (Laboratory) ግንባታ ጎበኙ።
Silti Wereda Silte Zone, Central Ethiopia
የስልጢ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሸምሴ ረዲ በወረዳው አሹቴ ቀበሌ በዳያስፖራው በተሳትፎና ድጋፍ እየተገነባ የሚገኘውን የአሹቴ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የቤተ-ሙከራ (Laboratory) ግንባታ ጎበኙ።
Education 📅 August 23, 2026

የስልጢ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሸምሴ ረዲ በወረዳው አሹቴ ቀበሌ በዳያስፖራው በተሳትፎና ድጋፍ እየተገነባ የሚገኘውን የአሹቴ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የቤተ-ሙከራ (Laboratory) ግንባታ ጎበኙ።

የቤተ-ሙከራ ግንባታ ምልከታ የስልጢ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሸምሴ ረዲ በወረዳው አሹቴ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እየተገነባ የሚገኘውን የቤተ-ሙከራ (Laboratory) ግንባታ ጎብኝተው የሥራውን ሂደት ተመልክተዋል።

የቤተ-ሙከራ ግንባታ ምልከታ የስልጢ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሸምሴ ረዲ በወረዳው አሹቴ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እየተገነባ የሚገኘውን የቤተ-ሙከራ (Laboratory) ግንባታ ጎብኝተው የሥራውን ሂደት ተመልክተዋል። በጉብኝቱም የግንባታው አፈጻጸም፣ የሥራው ጥራት እና በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ እየተደረገ ያለው ጥረት ተመልክተው ከቀበሌው ከተውጣጡ የማህበረሰብ ክፍሎች ውይይት በማድረግ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት የሚሆንበትን አቅጣጫ መክረዋል። የቤተ-ሙከራው ግንባታ ሲጠናቀቅ ተማሪዎች በተግባር የተደገፈ ትምህርት እንዲያገኙ፣ የሳይንስ ትምህርትን በተሻለ ሁኔታ እንዲማሩ እና የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል የሚያግዝ እንደሆነ ተነግሯል። የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሸምሴ ረዲ የዳያስፖራው ተሳትፎ በትውልድ አካባቢ የትምህርት መሠረተ ልማትን በማጠናከር ተማሪዎች በተግባር የተደገፈ ትምህርት እንዲያገኙ የሚያግዝ ተግባራዊ አስተዋጽኦ ነው ሲሉ ተናግረዋል። የአሹቴ ዳያስፖራ ያሳየው ተሳትፎ ለትውልድ አካባቢ ልማት ትልቅ አቅም መሆኑን በማሳየት፣ ሌሎችም በትምህርትና በሌሎች የልማት ዘርፎች ተሳትፎአቸውን እንዲያጠናክሩ ምሳሌ የሚሆን ነው ብለዋል። ነሃሴ 17/2018/ስልጢ ወረዳ ኮሚኒኬሽን)

Thank you for reading. View All News