Silti Wereda Silte Zone, Central Ethiopia

የስልጢ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ መልእክት

አቶ ከሚል ከድር

የስልጢ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ

Welcome Message

ውድ የስልጢ ወረዳ ነዋሪዎች፣ የፓርቲ አባላት፣ ደጋፊዎች እና ክቡራን እንግዶች፣ ወደ ስልጢ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኦፊሴላዊ ድረ-ገጽ በደህና መጡ።

በወረዳችን ባለፉት የለውጥ ዓመታት በፓርቲያችን ብልፅግና የፊት መሪነት በተከናወኑ ዘርፈ ብዙ ተግባራት በፖለቲካ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ዘርፎች ላይ ጅምር የለውጥ እንቅስቃሴና መነቃቃት ማስመዝገብ ተችሏል። ይህ ጅምር የለውጥ ጉዞ መዳረሻው እንደ ሀገር ያስቀመጥነውን "ሁለንተናዊ ብልፅግናዋን ያረጋገጠች አፍሪካዊት የብልፅግና ተምሳሌት የሆነች ኢትዮጵያን" እውን ሆና እስከ ማየት ሲሆን፣ ይህንን ጉዞ ከዳር ለማድረስ የሕዝባችንን ተሳትፎና ባለቤትነት ይበልጥ በማጠናከር ላይ እንገኛለን።

እንደ ወረዳችንም ይህንን ሀገራዊ ራዕይን እዉን ለማድግ ግብ ጥለን በመነሳት የፓቲና መንግስት ተግባራትን በየደረጃዉ በሚገኙ አደረጃጀቶች በማሳለጥ እና ወደ ዉጤት በመቀየር ወረዳችንን የተሞክሮ እና የብልፅግና ተምሳሌት ለማድግ ያሉን እምቅ አቅሞችን የመለየት እና የመጠቀም እንዲሁም መላዉ ኣባላት እና ደጋፊዎቻችን ከጎናችን በማሰለፍ የተለያዩ ችግር ፊቺ የሆኑ እንሼቲቮችን ቀርፆ በማዉረድ የማህበረሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እና በሂደቱም የፓርቲችንን ህዝባዊ ቅቡልነት ለማላቅ በተሰሩ ስራዎች አበረታች ዉጤቶችን ማስመዝገብ ተችሏል፡፡

እንደ ወረዳችን ባለፉት የለዉጥ ዓመታት በአባላት እና አደረጃጀቶች መሪነት የፓርቲያችን ብልፅግና የበላይነት እንዲረጋገጥ የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን ማሳካት ተችሏል፡፡ በ2018 ዓ.ም 7ኛውን ሀገራዊ እና ክልላዊ ምርጫን ከቅድመ-ዝግጅት እስከ ድኅረ ምርጫ ድረስ በጠንካራ አደረጃጀት እና አባላት ተሳትፎ በተሰራዉ ዘርፈ ብዙ ስራ በምርጫው የተቀመጡ ሁለት ግቦችን በማሳካት በወረዳችን በሚገኙ 28ቱም ቀበሌዎች በሚገኙ ምርጫ ጣቢያዎች ፓርቲያችን ብልፅግና መንግስት ለመመስረት የሚያስችለውን ከፍተኛ ድምፅ እንዲያገኝ ማሳካት የተቻለበት አግባብ በቀጣይ ስራዎቻችንም ለሁለንተናዊ ብልፅግና ጉዟችን ስኬታማነት የጋራ ጥረት እና ተሳትፎ ተጠናክረው ሊሄዱ የሚገባቸው ተግባራት ናቸው፡፡

በተለይም ወረዳችንን የብልፅግና እና የተሞክሮ ማዕከል፣ የተረጋጋና ሠላማዊ እንዲሁም የሥራ ፈጠራና የጠንካራ ወንድማማችነትእና እህትማማችነት ማዕከል አድርጎ ለመገንባት ታቅደዉ እየተከናወኑ በሚገኙ ተግባራት ተጨባጭ ዉጤቶች እየተመዘገቡ ይገኛል በቀጣይም ለተሻለ የማህበረሰብ ተጠቃሚነትም አቅዶ የማከናወኑ ተግባር ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡ ሁሉም የፓርቲና የመንግስት ተግባራት በአባላት መሪነት እና በአደረጃጀቶች አማከኝነት እንዲሳለጡ በማድረግ የመፈፀም ብቃት በማሻሻል አበረታች ስራዎችን መስራት ተችሏል በቀጣይም ተጠናክሮ ይቀጥላል ከዚህ ጎንለጎን በየጊዜዉ ወረዳዊ እና ከባቢያዊ ነባራዊ ሁኔታዎችን ሳይንሳዊ በሆነ አግባብ በመተንተንና ፈጣን ስትራቴጂያዊ ምላሽ በመስጠት ለብልፅግና ጉዟችን ምቹ ፖለቲካዊ ሁኔታን ለመፍጠር ታቅዶ በተሰሩ ስራዎች በርካታ ዉጤቶችን ማስመዝገብ ተችሏል በቀጣይም ተግባሩ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል

የአመራሩንና አባሉን የክህሎት ክፍተት ለመሙላት እና የአስተሳሰብና የተግባር አንድነቱን ለማረጋገጥ በሚያስችሉ ወቅታዊ እና ሀገራዊ ርእሰ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት በማድረግ የአመራሩን እና አባላትን ንድፈ-ሀሳባዊ እውቀታቸውንና የክህሎት አቅማቸውን የማሳደግ እንዲሁም በየጊዜው ወቅቱን የጠበቀ የህዝብ ውይይት በማድረግ በሁሉም መስክ የህዝብ ተሳትፎ እንዲጎለብትና ፍትሐዊ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ በማነሳሳት ህዝቡ በፓርቲው ላይ ያለውን ቅቡልነት ማሳደግ፣ የአመራሩን፣ የአባሉንና የህዝቡን የዕርስ በርስ ግንኙነት ለማጎልበት ሰፊ ስራ ተሰርቷል በቀጣይም የእቅድ አካል ተደርጎ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል

በወረዳችን በፓርቲው የተቀረፁ የልማት ኢኒሼቲቮችን ሀድ ኢንጫቆ ሆሽት ማሽን፡በዘራማይ የትራከቢ፡ ቦሽት ጣሰ ሰኜ ሴፍትኔት ወገሬት፡ የጎዳና ግብርናና የገጠር ኮሪደር፡ኢትዮ ኮደርስ፡ፋይዳ መታወቂያ፤አንድ ከተማ አንድ ፕሮጀክት፡እንደት ተንበር፤የአፊየ ዲጋየ በቤደረ፡አጅስ ኡስቤ ላቁምሲነ፡አንድ ቤተሰብ ለ1 ሚሊሻ አልባሳት፡ያሽር ጡልት ተሸኜንከ እና ሌሎችንም በአግባቡ በመምራትና በማስተባበር የህብረተሰባችንን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ፣ በወረዳችን መልካም አስተዳደር እንዲሰፍንና የተቋማት አገልግሎት አሠጣጥ እንዲሻሻል በማድረግ የህዝብ ቅሬታን በመፍታት የህዝብ እርካታን አንድ ደረጃ ከፍ ማድግ ተችቷል

በአጠቃላይ ባለፉ የለዉጥ ዓመታት በወረዳችን በሁሉም ዘርፍ በተሰሩ ዘርፈ ብዙ ስራች የማህበረሰቡን ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ቀደም ሲል ከነበረበት ከፍተኛ መሻሻል የታየበት መሆኑ ፡-ላስቀመጥነዉ የሁለንተናዊ ብልፅግና ጉዞ ጠንካራ መሳካት ጠንካራ መሰረት ነዉና በቀጣይም የተመዘገቡ ውጤቶችንናየተገኙ መልካም ተሞክሮዎችን በማስቀጠል እና በጉዟችን የነበሩ ጉድለቶችን ለይቶ በማረም ና ጠንካራ የፓርቲ ተቋም በመገንባት የህዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ዋነኛው የትኩረት አቅጣጫችን አድርገን ለተፈፃሚነቱ ሌት ተቀን የምንተጋ ይሆናል፡፡