Silti Wereda Silte Zone, Central Ethiopia

ራዕይ

ራዕይ

ሀ) እንደ ሀገር የተያዘዉን በ2024 ኢትዮጵያን አፍሪካዊት የብልጽግና ተምሳሌት የማድረግ ግብን ለማሳካት ሁላቀፍ ርብርብ በማድረግ የተሞክሮ እና የብልፅግና ተምሳሌት የሆነች ወረዳ መፍጠር ነዉ፡፡
በፖለቲካዊ፡ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ዘርፍ ላይ እንደ ሀገር የተቀመጡ ስትራቲጂያዊ ግቦችን ተከትለን በመስራት ለ) እንደ ሀገር የተቀመጠዉን ጠንካራ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ቅቡልነት ያለው፣ ዘላቂ ሀገረ-መንግሥትና ማህበረሰባዊ አንድነት ለመገንባት የሚያስችሉ ስራዎችን እንደ ወረዳችን በመስራት በሀገረ መንግስት ግንባታዉ ላይ የበኩላችንን ሚና መወጣት
ሐ)ወረዳችን ላይ ያሉ አማራጮችን በሙሉ አሟጦ በመጠቀም የማህበረሰባችንን ልማትና ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ አካታች የኢኮኖሚ ሥርዓት መገንባት
መ) የወረዳችንን ማህበረሰብ ሁለንተናዊ ብልፅግናን የሚያሰፍን ማኅበራዊ ልማትን ማረጋገጥ
ረ) ሀገራዊ ክብርንና ጥቅምን ከፍ ሊያደርጉ የሚችሉ ስራዎችን አቅዶ መስራ እና በተለያዩ ጊዜያት የሚከበሩ ኩነቶችን ወቅቱን ጠብቆ በደማቅ ሁኔታ እያከበሩ አስተሳሳሪ እና ሀገራ ገዢ ትርክት ግንባታ ላይ የበኩላችንን አስታዉፆ ማበርከት ነዉ ።