Silti Wereda Silte Zone, Central Ethiopia

ተልዕኮ

ተልዕኮ

 የውስጠ ፓርቲ አንድነትና ዴሞክራሲን በማጠናከር እና የወረዳችንን ማህበረሰብ ሁለንተናዊ ብልጽግና የሚያረጋግጡ የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና በማህበረሰባችን ዘንድ ጠንካራ ወንድማማችነትና እኅትማማችነት እንዲጎለብት በማቀድ እና በመፈፀም በኢትዮጵያ ሕዝቦች ዘንድ ቅቡልነት ያለው ዴሞክራሲያዊ ህብረ-ብሔራዊ ፌደራላዊ ሥርዓት በመገንባት ረገድ የፊት መሪነት ሚናን መጫወት ነው።
 በየደረጃው የሚገኙ የፓርቲ አደረጃጀቶች ዘመናዊ የዕቅድ አዘገጃጀት፣ የሪፖርት ና የክትትል ሥርዓት በመዘርጋት የህዝብን ተጠቃሚነት በተጨባጭ ማረጋገጥ።
 የፓርቲችንን የአሰራርና አደረጃጀት መመሪያ ማዕቀፍ ተከትለን ጥራት ያላቸዉ አባላትን በማፍራት እንደ ወረዳችን ባለግዙፍ አባል ጠንካራ የፓርቲ ተቋም መገንባት
 ተለዋዋጭ የፖለቲካ ነባራዊ ሁኔታዎችን በሳይንሳዊ መንገድ በመተንተን፣ ወቅታዊና ስልታዊ ምላሾችን ተግባራዊ በማድረግ ለብልፅግና ጉዟችን ምቹና አስተማማኝ የፖለቲካ ምህዳር መፍጠር።
 የፓርቲያችንን አመራር እና አባላት የንድፈ-ሀሳብና የክህሎት ብቃት ሊያሳድጉ የሚችሉ ተከታታይነት ያላቸዉ የአቅም ግንባታ ስራዎችን መስራት
 ቀጣይነት ባለው መልኩ ውጤት ተኮር የሕዝብ ንቅናቄ ሥራዎችን በማከናወን ሁለንተናዊ የህዝባችንን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እና የፓርቲውን ቅቡልነት ማላቅ፡፡
 በፓርቲው የተቀረጹ ታላላቅ የልማት ኢኒሼቲቮችን በውጤታማነት በመምራት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት በተግባር ማረጋገጥ
 የወንድማማችነት/ እህትማማችነት እሴትና የህዝቦችን አንድነት ሊያጎልብቱ የሚችሉ ስራዎችን መስራት፤
 የፓርቲውን አደረጃጀትና አሰራሮችን በማዘመንና ተግባራዊ በማድረግ የፓርቲውን ተቋማዊ ጥንካሬ ማረጋገጥ
 የሀገሪቱን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፖሊሲዎችን በብቃት መቅረፅ፣ ማቀድና መፈፀም የሚችል አመራር በየደረጃው ማፍራትና ማብቃት የሚያስችሉ ተግባራትን ተፈፅሟል፣
 ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር በትትብር እና በፉክክር ማእቀፍ በመስራት የዳበረ ፤አካታች እና አሳታፊ የዲሞክራሲ ምህዳር ማሳደግ
 የሴቶች እና ወጣቶች ክንፍ አደረጃጀቶችን በማጠናከር ፖለቲካዊ ተሳትፎና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ማሳደግ
 የተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አዉታሮችን በመጠቀም የፓርቲያችን እሳቤዎች፣ ዓላማዎችና ስኬቶችን ማስረፅ፤
 ጠንካራ የሰው ሐብት ልማት ፤የንብረት አያያዝና የፋይናንስ አስተዳደር ስርዓት በመዘርጋት የፓርቲውን የመፈጸም አቅም ማሳደግ
 በሁሉም ዘርፍ የሚገኙ ምርጥ ተሞክሮዎችን የመቀመርና የማስፋት ስራን መስራት