```blade ``` በስልጢ ወረዳ በቀርጠፍ ቀበሌ የጸደይ ሰብል (የሽምብራ) ዘር ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄደ!!!
Silti Wereda Silte Zone, Central Ethiopia
በስልጢ ወረዳ በቀርጠፍ ቀበሌ የጸደይ ሰብል (የሽምብራ) ዘር ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄደ!!!
Agriculture 📅 September 14, 2026

በስልጢ ወረዳ በቀርጠፍ ቀበሌ የጸደይ ሰብል (የሽምብራ) ዘር ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄደ!!!

~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~ መስከረም 04/2019 የስልጢ ወረዳ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን። በስልጢ ወረዳ የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት ለመጨመር የሚያስችል የጸደይ ሰብል (የሽምብራ) ዘር ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄዷል። በመርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የስልጤ ዞን ም/አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙበራ ከማል፦ የግብርና ልማት ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባና የአርሶ አደሩን የኑሮን ሁኔታ ለማሻሻል ገቢውን ለመጨመር የሚያስችል እንደሆነ በመግለፅ በአካባቢው ያለውን የዝናብ ሁኔታና የአፈር እርጥበትን በአግባቡ በመጠቀም የአርሶ አደሩን ህይወት የሚቀይሩ የግብርና አሰራሮችን ማስፋፋት እንደሚገባ ኃላፊው አስገንዝበዋል። የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ አኳያም የመኸር ምርት ከመጀመሩ በፊት የሚሰበሰብ በመሆኑ በቤተሰብ ደረጃ ሊከሰት የሚችለውን የምግብ እጥረት ማስቀረት የሚችል እና የፀደይ ሰብሎች በፍጥነት ስለሚደርሱ አርሶ አደሩ ምርቱን ገበያ ላይ በማቅረብ በአጭር ጊዜ ውስጥ ፈጣን የገንዘብ ገቢ እንዲያገኝም ያደርጋል ብለዋል። የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሸምሴ ረዲ በበኩላቸው፦ የጸደይ ሰብል ልማት አርሶ አደሩ በዓመት ከአንድ ጊዜ በላይ እንዲያመርትና የምግብ ዋስትናውን እንዲያረጋግጥ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸዋል። በተለይም የሽምብራ ዘር አነስተኛ ውኃ የሚፈልግ ፣ የአፈር ለምነትን የሚጨምርና በገበያ ላይ ከፍተኛ ተፈላጊነት ያለው በመሆኑ አርሶ አደሩን በአጭር ጊዜ ውስጥ አወጪና ትርፋማ የሚያደርግ ስትራቴጂካዊ ሰብል መሆኑን ተናግረዋል። በመርሃ ግብሩ ላይ የስልጤ ዞን ም/አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙበራ ከማል ፣ የስልጢ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሸምሴ ረዲ ፣ የስልጤ ዞን ግብርና መምሪያ ም/ኃላፊ አቶ ነጃ ሽፋ ፣ የስልጢ ወረዳ ም/አስተዳዳሪና የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብደላ መሀመድ ፣ የክልል፣የዞንና የወረዳ የግብርና ልማት አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም የቀርጠፍ ቀበሌና የአካባቢው አርሶ አደሮች በተግባር የዘር ስራውን ያስጀመሩ ሲሆን ፣ በተያዘው የጸደይ ወቅት የታቀደውን የምርት መጠን ለማሳካት የተቀናጀ ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግም ተገልጿል።

Thank you for reading. View All News