የስልጤ ዞን የበጎ ተግባር ቴክኒክ ኮሚቴ በስልጢ ወረዳ የበጎ ተግባር ሥራዎችን ተመለከተ
የስልጤ ዞን የበጎ ተግባር ቴክኒክ ኮሚቴ በስልጢ ወረዳ የበጎ ተግባር ሥራዎችን ተመለከተ
ነሐሴ 02/2018 ዓ.ም (ስልጢ ወረዳ ኮሚኒኬሽን) የስልጤ ዞን የበጎ ተግባር ቴክኒክ ኮሚቴ በስልጢ ወረዳ በመገኘት በክረምት ወቅት በበጎ ተግባር የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን በመመልከት ድጋፍና ክትትል አድርጓል።
ኮሚቴው በወረዳው በመገኘት በክረምቱ ወቅት በህብረተሰቡ፣ በተለያዩ ተቋማትና በበጎ ፈቃደኞች ተሳትፎ የተከናወኑ የበጎ ተግባር ሥራዎችን በመስክ ተመልክቷል።
የተከናወኑ ሥራዎች ከተያዙ ዕቅዶች አንፃር ያላቸው አፈጻጸም፣ የሥራዎቹ ጥራትና ቀጣይነት ተገምግሟል።
በተጨማሪም በአፈጻጸም ሂደት የታዩ ጠንካራ ጎኖችና መሻሻል የሚፈልጉ ጉዳዮች ተለይተው ለቀጣይ ሥራ አቅጣጫ ተሰጥቷል።
በወረዳው የተጀመሩ የበጎ ተግባር ሥራዎች በጥራት እንዲጠናቀቁና የህብረተሰቡ ተሳትፎ እንዲጠናከር በትኩረት እንዲሰሩ ኮሚቴው አሳስቧል።
በአጠቃላይ የቴክኒክ ኮሚቴው የመስክ ምልከታና ክትትል በወረዳው የበጎ ተግባር አፈጻጸምን ለማጠናከር፣ የተጀመሩ ሥራዎችን በጥራት ለማስቀጠልና በበጎ ተግባር የሚገኘውን የህብረተሰብ ተሳትፎ ይበልጥ ለማሳደግ ጠቃሚ መሆኑ ተገልጿል።