```blade ``` የስልጢ ወረዳ ካቢኔ የቀድሞ እንቨስትመንቶችን አፈፃፀም በመገምገም አዳዲስ የእንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን መርምሮ አፀደቀ
Silti Wereda Silte Zone, Central Ethiopia
የስልጢ ወረዳ ካቢኔ የቀድሞ እንቨስትመንቶችን አፈፃፀም በመገምገም አዳዲስ የእንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን መርምሮ አፀደቀ
investment 📅 August 11, 2026

የስልጢ ወረዳ ካቢኔ የቀድሞ እንቨስትመንቶችን አፈፃፀም በመገምገም አዳዲስ የእንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን መርምሮ አፀደቀ

የስልጢ ወረዳ ካቢኔ የቀድሞ እንቨስትመንቶችን አፈፃፀም በመገምገም አዳዲስ የእንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን መርምሮ አፀደቀ

የስልጢ ወረዳ ካቢኔ በወረዳው ከዚህ ቀደም የተሰማሩ የእንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን አፈፃፀም በዝርዝር በመገምገም፣ በቀጣይ የሚተገበሩ አዳዲስ የእንቨስትመንት እቅዶችን መርምሮ አፅድቋል።

ነሐሴ 03/2018(ስልጢ ወረዳ ኮሚኒኬሽን)

መድረኩን የስልጢ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሸምሴ ረዲ የመሩት ሲሆን፣ የወረዳው አስተዳደር ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አህባብ መህሙድ በወረዳው ከዚህ ቀደም የተሰማሩ እንቨስትመንቶችን አፈፃፀም በተመለከተ ዝርዝር ሪፖርት አቅርበዋል።

በግምገማው የእንቨስትመንት ፕሮጀክቶቹ የደረሱበት ደረጃ፣ የተሰማሩበት ዘርፍ፣ ያመጡት የሥራ ዕድልና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም፣ እንዲሁም በአፈፃፀም ሂደት ያጋጠሙ ችግሮች በስፋት ተመልክተዋል።

ከዚህ በፊት የተፈቀዱ ፕሮጀክቶች ወደ ተግባር በሚገቡበት ሂደት የታዩ መሻሻሎችን በማጠናከር፣ ያልተፈፀሙ ወይም ከታቀደላቸው ጊዜና ዓላማ የዘገዩ ፕሮጀክቶች ላይ ተገቢው ክትትልና ድጋፍ እንዲደረግ አቅጣጫ ተቀምጧል።

ወረዳው ሰፊ የኢንቨስትመንት አማራጭ፣ የሚገኙ የተፈጥሮና የሰው ሀብቶች፣ የግብርና ምርት አቅም እና የተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች መኖራቸው በጥንካሬ ተጠቅሷል።

ይህም ስልጢ ወረዳን በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ለመሰማራት አመቺ እና ተመራጭ የኢንቨስትመንት መዳረሻ እንድትሆን የሚያስችሉ እድሎች እንዳሏትም ጭምር ተገምግሟል።

የታዩ ጉድለቶችና ተግዳሮቶች በሌላ በኩል አንዳንድ ፕሮጀክቶች በተፈቀደላቸው ጊዜ መሠረት ወደ ሥራ አለመግባታቸው፣ የፕሮጀክት አፈፃፀም ክትትል ክፍተቶች፣ የባለሀብቶች ተጠያቂነትን በተገቢው ደረጃ አለመከታተል እና ከባለሀብቶች ጋር በሚደረግ ቅንጅታዊ ሥራ ላይ ያሉ ክፍተቶች ተመላክተዋል።

እነዚህ ጉድለቶች እንዳይደገሙ ከፕሮጀክት ምርጫና ፍቃድ አሰጣጥ ጀምሮ እስከ ትግበራና ውጤት ማምጣት ድረስ ያለው ሂደት በተጠናከረ ክትትል እንዲመራ አቅጣጫ ተቀምጧል።

የወረዳው ካቢኔ አባላት በውይይታቸው እንቨስትመንት ለወረዳው የኢኮኖሚ እድገት፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራ እና ለመንግሥት ገቢ ማሳደግ የሚኖረውን ሚና በማጉላት፣ እያንዳንዱ ፕሮጀክት በአፈፃፀሙ የሚለካ እንጂ በፈቃድ ደረጃ ብቻ የሚቆጠር እንዳይሆን አስገንዝበዋል።

ካቢኔው በተለይም ባለሀብቶችን ከመሳብ ባለፈ የተፈቀዱ እንቨስትመንቶች በተጨባጭ ወደ ምርትና አገልግሎት እንዲገቡ፣ ለወጣቶችና ለማህበረሰቡ የሥራ ዕድል እንዲፈጥሩ እና ለአካባቢው ኢኮኖሚ የሚታይ አስተዋፅኦ እንዲኖራቸው ተገቢው ክትትል እንዲደረግ አሳስቧል።

አዳዲስ የእንቨስትመንት ፕሮጀክቶችም ሲመረጡ የወረዳውን የተፈጥሮ ሀብት፣ የግብርና ምርት፣ የገበያ አቅም፣ የሥራ ዕድል ፈጠራ እና የአካባቢውን ልማት የሚያገናዝቡ መሆናቸው በቅድሚያ እንዲረጋገጥ አቅጣጫ ተሰጥቷል።

አዳዲስ ፕሮጀክቶች ተመርምረው ፀደቁ

በመድረኩ ከቀድሞ እንቨስትመንቶች ግምገማ በተጨማሪ አዳዲስ የእንቨስትመንት ሀሳቦች ቀርበው በካቢኔው በዝርዝር ተመርምረዋል።

ፕሮጀክቶቹ ከወረዳው የልማት አቅጣጫ ጋር ያላቸው ተጣጣሚነት፣ የኢኮኖሚ ጥቅም፣ የሥራ ዕድል ፈጠራ አቅም፣ የሀብት አጠቃቀምና የትግበራ አቅም በመመርመር ተገቢ የሆኑት እንዲፀድቁ ተወስኗል።

የስልጢ ወረዳ ካቢኔ በቀጣይ የእንቨስትመንት ሥራው ትኩረት የሚሰጠው የፕሮጀክቶችን ቁጥር በማሳደግ ብቻ ሳይሆን፣ የተፈቀዱ ፕሮጀክቶች በፍጥነት ወደ ተግባር እንዲገቡና የሚጠበቅባቸውን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ውጤት እንዲያመጡ ማድረግ ላይ እንደሚሆን ገልጿል።

በዚህም የባለሀብቶች የሚያጋጥሟቸውን ተግዳሮቶች በፍጥነት መፍታት፣ የአገልግሎት አሰጣጥን ማቀላጠፍ፣ የፕሮጀክቶችን አፈፃፀም በየደረጃው መከታተል እና ተጠያቂነትን ማጠናከር ቀጣይ ትኩረቶች እንደሚሆኑ ተጠቁሟል።

ወረዳዋ ያላትን የተፈጥሮ ሀብት፣ የግብርና ምርት፣ የሰው ሀብትና የገበያ አቅም በአግባቡ በማስተባበር ለተለያዩ የእንቨስትመንት ዘርፎች ምቹ ሁኔታ ያላት በመሆኗ በዞኑ ውስጥ ተመራጭ የእንቨስትመንት መዳረሻ ለመሆን ትልቅ አቅም እንዳላት ተገልጿል።

በመጨረሻም ካቢኔው አዳዲስ እንቨስትመንቶች በጥናትና በአዋጭነት ምርመራ እንዲመረጡ፣ የተፈቀዱትም በተያዘላቸው ጊዜ ወደ ሥራ እንዲገቡ እና የወረዳውን ኢኮኖሚ በሚያነቃቃ መልኩ እንዲተገበሩ አቅጣጫ በመስጠት መድረኩን አጠናቋል።

Thank you for reading. View All News